የሩሲያ እና አሜሪካ የልዑካን ቡድን ዛሬ ማክሰኞ በሳዑዲ አረቢያ ይገናኛሉ

ሰብስክራይብ
የሩሲያ እና አሜሪካ የልዑካን ቡድን ዛሬ ማክሰኞ በሳዑዲ አረቢያ ይገናኛሉ በሪያድ በሚደረገው ስብሰባ የሞስኮን የልዑካን ቡድን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ እና የክሬምሊን ረዳት ዩሪ ኡሻኮቭ እንደሚመሩ ክሪምሊን ቀደም ሲል ተናግሯል። የምዕራቡ ዓለም መገናኛ ብዙኃን እንደዘገቡት የአሜሪካው ልዑካን ቡድን በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ፣ በብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ሚካኤል ዋልትዝ እና በመካከለኛው ምስራቅ ልዩ መልዕክተኛ ስቲቨን ዊትኮፍ ይመራል። የዩክሬን ድርድር፣ የፕሬዝዳንት ፑቲን እና ትራምፕ የፊት ለፊት ግኑኝነት ዝግጅት እና የሩሲያ እና የአሜሪካን ግንኙነት ሙሉ በሙሉ ወደነበረበት መመለስ በአጀንዳው ላይ ከተካተቱት ጉዳዮች መካከል እንደሆኑ ክሬምሊን አስታውቋል። ይህን ትልቅ ሁነት በስፑትኒክ አፍሪካ ይከታተሉ! ምስሉ በሰው ሰራሽ አስተውህሎት የመነጨ ነውበእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0