ኢትዮጵያ እና ቻይና የፍትህ ዘርፍ ትብብራቸውን በማሳደግ ዙርያ ተወያዩ

ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ እና ቻይና የፍትህ ዘርፍ ትብብራቸውን በማሳደግ ዙርያ ተወያዩ በቻይና የፍትህ ሚኒስትር ሄ ሮንግ የተመራ ልዑክ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብቷል። ለልዑኩ አቀባበል ያደረጉት የፍትህ ሚኒስትር ዴኤታ በላይሁን ይርጋ፤ ጉብኝቱ በሁለቱ የብሪክስ አባል ሀገራት መካከል ያለውን የቆየ ትብብር፤ በተለይም በሕግ እና በፍትህ ዘርፍ የበለጠ ለማጠናከር ጠቃሚ እንደሆነ ተናግረዋል። ሚኒስትር ሄ ሮንግ ከፍትህ ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች፣ ከፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና ከፌደራል የጠበቃ ማህበር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። ሚኒስትሩ በሕግ እና በፍትህ ጉዳዮች ዙርያ ትብብር ማድረግ የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት፤ ከኢትዮጵያ የፍትህ ሚኒስትር ሃና አርአያስላሴ ጋር እንደሚፈራረሙ፤ ከፍትህ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0