ኢትዮጵያ በስንዴ ልማት ያስመዘገበችው ስኬት ለአፍሪካ የምግብ ሉዓላዊነት ጥረት ምሳሌ እንደሚሆን ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ጠቆሙ

ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ በስንዴ ልማት ያስመዘገበችው ስኬት ለአፍሪካ የምግብ ሉዓላዊነት ጥረት ምሳሌ እንደሚሆን ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ጠቆሙፕሬዝዳንቱ ይህን ያሉት፤ አዲስ አበባ እየተካሄደ በሚገኘው የመስኖ ልማትና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ምርታማነትን ትኩረቱ ባደረገው ጉባዔ ላይ ነው። በጉባዔው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ፕሬዝዳንት ታዬ፤ ኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አመራር ሰጭነት፤ በአፍሪካ ማህብረሰብ አቀፍ የግብርና ልማት ሽግግርን እየመራች ነው ብለዋል። የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብርን ለአብነት ያነሱት ፕሬዝዳንቱ፤ 40 ቢሊየን ችግኝ በመትከል የደን ሽፋንን ማሳደግ እንደተቻለ እና በአትክልትና ፍራፍሬ ልማት በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎች የምግብ ዋስትናቸውን እንዲያረጋገጡ መቻሉን ጠቅሰዋል። የሀገሪቱን የስንዴ ልማት ተነሳሽነት በተመለከተ፤ ከውጭ የሚገባ ስንዴን በማቆም የስንዴ ምርት ፍጆታዋን በራሷ አቅም ማምረት ችላለች ብለዋል። ይህም አፍሪካ ራሷን መመገብ እንደምትችል ማረጋገጫ ነው ሲሉ አስረግጠዋል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0