የደቡብ አፍሪካ ባለስልጣናት በዘረኝነት የሚወነጅላቸው ኤለን መስክ የሀገሪቱን የሕግ ስርዓት በአግባቡ እንዲረዳ ጠየቁ

ሰብስክራይብ
የደቡብ አፍሪካ ባለስልጣናት በዘረኝነት የሚወነጅላቸው ኤለን መስክ የሀገሪቱን የሕግ ስርዓት በአግባቡ እንዲረዳ ጠየቁ የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት የፕሬስ ሴክሬታሪ ቪንሴንት ማግዌኒያ፤ ኤለን መስክ በኢኮኖሚ ነፃነት ተዋጊዎች የፖለቲካ ፓርቲ መሪ ጁሊየስ ማሌማ ላይ የሰነዘረውን ትችት ተከትሎ፤ አሜሪካዊው የሥራ ፈጣሪ “እራሱን ሰብሰብ” እንዲያደርግ እና ስለ ደቡብ አፍሪካ የሕግ ስርዓት እንዲያነብ ጠይቀዋል። ማሌማ ዓመፅ እና ነጮች እንዲገደሉ ሲቀሰቅስ የሚያሳይ ቪዲዮ በኤክስ የትስስር ገጽ ላይ ከተሰራጨ በኋላ፤ መስክ የኢኤፍኤፍ መሪው ዓለም አቀፍ ወንጀለኛ ተብሎ መፈረጅ አለበት ብሏል። መስክ በጉዳይ ላይ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ አስተያየት እንዲሰጡም ጠይቋል። "እባካህን እራስህን ሰብስብ! ቪዲዮው የቆየ ነው፤ ማረጋገጥ ትችላለህ። በእነዚህ ሰዎች ወይም በመግለጫቸው ምክንያት ነጮች አልተገደሉም። ቅስቀሳን የምንዋጋበት ሕጋዊ መሳሪያዎች አሉን። ሕጋዊ ስርዓታችንን በአግባቡ ልታውቅ ይገባል" ሲሉ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት የፕሬስ ሴክሬታሪ ቪንሰንት ማግዌንያ ለመስክ አስተያየት ምላሽ ሰጥተዋል። ቢልዬነሩ የደቡብ አፍሪካ የመሬት ባለቤትነት ሕግ ዘረኛ ነው ከማለቱ ጋር በተያያዘ፤ በሀገሪቱ ዙሪያ ያለውን የተዛባ መረጃ አስመልክቶ ራማፎሳ ከመስክ ጋር መነጋገራቸው የሚታወስ ነው።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0