የናሚቢያ የመጀመሪያ ፕሬዝዳንት ሳም ኑጆማ በ95 አመታቸው አረፉየናሚቢያ ነፃነት ጀግና እና ሀገሪቷን ከመሰረቱ አባቶች አንዱ የነበሩት ሳም ኑጆማ ከሶስት ሳምንት የሆስፒታል ቆይታ በኋላ በትላትናው እለት ማረፋቸው ታውቋል። ፕሬዝዳንት ኑንጎሎ ምቡምባ በመግለጫቸው እንዳሉት ፤ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ከህመማቸው ጋር ሲታገሉ ቆይተዋል። የፕሬዝዳንት ኑጆማ የህይወት ስኬቶች ፦ ⏺ የተወለዱት ከገበሬ ቤተሰቦቻቸው በጎርጎሮሳዊያኑ ግንቦት 12, 1929 ሲሆን አስር ልጆች ላሏቸው ቤተሰቦቻቸው የበኩር ልጅ ነበ።⏺ በመዲናዋ ዊንድሆክ አቅራቢያ በሚገኝ ባቡር ላይ የፅዳት ሰራተኛ ነበሩ ፤ በዛን ወቅት የማታ ትምህርት ላይ የነፃነት አክቲቪስቶችን ተዋዉቀዋል።⏺ በጎርጎሮሳዊያኑ 1960 የተቋቋመውን እና በ1966 የትጥቅ ትግል የጀመረውን የስዋፖ (SWAPO) የነፃነት እንቅስቃሴ በአጋርነት መስርተዋል። ⏺ በመጀመሪያው የአለም ጦርነት ወቅት ደቡብ አፍሪካ ከጀርመን የናሚቢያን ግዛት የተረከበች ሲሆን ፤ ናሚቢያ ከደቡብ አፍሪካ ነፃነቷን ካወጀች ከጎርጎሮሳዊያኑ 1990 ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ዙር ኑጆማ አስተዳድረዋት ነበር። ⏺ ኑጆማ ፤ በጎርጎሮሳዊያኑ 2021 ጀርመን በናሚቢያ በሚገኙ በአስር ሺዎች በሚቆጠሩ የሄሬሮ እና ናማ ነባር ህዝቦች ላይ ለፈፀመችው እና የ20ኛው ክፍለ ዘመን የመጀመሪያው የዘር ማጥፋት ተብሎ የሚቆጠረው የጅምላ ግድያ የከፈለችው የአንድ ቢሊዩን ዩሮ ካሳ በቂ አይደለም በማለት ተናግረው ነበር።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የናሚቢያ የመጀመሪያ ፕሬዝዳንት ሳም ኑጆማ በ95 አመታቸው አረፉ
የናሚቢያ የመጀመሪያ ፕሬዝዳንት ሳም ኑጆማ በ95 አመታቸው አረፉ
Sputnik አፍሪካ
የናሚቢያ የመጀመሪያ ፕሬዝዳንት ሳም ኑጆማ በ95 አመታቸው አረፉየናሚቢያ ነፃነት ጀግና እና ሀገሪቷን ከመሰረቱ አባቶች አንዱ የነበሩት ሳም ኑጆማ ከሶስት ሳምንት የሆስፒታል ቆይታ በኋላ በትላትናው እለት ማረፋቸው ታውቋል። ፕሬዝዳንት ኑንጎሎ ምቡምባ... 09.02.2025, Sputnik አፍሪካ
2025-02-09T17:20+0300
2025-02-09T17:20+0300
2025-02-09T17:44+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2025
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий