የሩሲያው ቅንጡ የመኪና ብራንድ ኦሩስ የኢትዮጵያን ባለስልጣናት ሊስብ ይችላል ሲሉ በሩሲያ የኢትዮጵያ አምባሳደሩ ተናገሩ

ሰብስክራይብ
የሩሲያው ቅንጡ የመኪና ብራንድ ኦሩስ የኢትዮጵያን ባለስልጣናት ሊስብ ይችላል ሲሉ በሩሲያ የኢትዮጵያ አምባሳደሩ ተናገሩ "መኪናውን አይቼዋለሁ፤ በእርግጥም ቅንጡ ነው። ከፍተኛ እና መሀከለኛ ገቢ ያላቸው ኢትዮጵያውያንን ፍላጎት ሊስብ ይችላል፤ በተለይም በንግድ አለም ውስጥ ያሉትን" ሲሉ በሩሲያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ገነት ተሾመ ጅሩ ተናግረዋል። የገበያ ትስስር እንዲፈጠር በተገቢው መልኩ መተዋወቅ አለበትም ብለዋል አምባሳደሩ።በመኪና ምርት ዙሪያ የሚደረግን ትብብር አስመልክቶ፤ ከሩሲያ የመኪና አምራቾች ጋር እየተደረገ ያለ ውይይት መኖሩን አምባሳደሩ ጠቁመዋል። ኦራል እና አዝ የተሰኙ የመኪና አምራቾች ተወካዮቻቸውን ወደ ኢትዮጵያ በመላክ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ አጋሮቻቸው ጋር የገበያ ጥናት እንደሰሩ እና በኢትዮጵያ ውስጥ የመኪና መገጣጠሚያን ለመክፈት የረጅም ጊዜ እቅድ መያዛቸውን ገልጸዋል።ይህ በእንዲህ እንዳለ በኢትዮጵያ የታክሲ አገልግሎት ውስጥ ከፍተኛ ስም እና ድርሻ ያለው ላዳ፤ ወደ የኤሌትሪክ የሚደርገው ሽግግር በያዝነው የጎርጎሮሳውያኑ አመት መጨረሻ ይጀመራል ብለዋል። "ከነዳጅ ወደ ኤሌክትሪክ የሚደረገው ሽግግር እንደተጠናቀቀ ድርጅቱ የመኪና ምርቱን ይጀምራል" ሲሉ አምባሳደሩ አረጋግጠዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0