የዳንጎቴ ነዳጅ ማጣሪያ ወደ ሳውዲ አረቢያ የጀት ነዳጅ በመላክ አዲስ ምእራፍ አስመዘገ

ሰብስክራይብ
የዳንጎቴ ነዳጅ ማጣሪያ ወደ ሳውዲ አረቢያ የጀት ነዳጅ በመላክ አዲስ ምእራፍ አስመዘገ የዳንጎቴ ግሩፕ ፕሬዝዳንት አልሀጂ አሊኮ ዳንጎቴ እንዳሉት ፤ ማጣሪያው ሁለት ጭነት የጀት ነዳጅ በአለም ትልቁ የነዳጅ አምራች ወደ ሆነው የሳውዲው አራምኮ መላኩን ለሀገር ውስጥ ሚዲያዎች አሳዉቀዋል። ዳንጎቴ በማጣሪያው እድገት መኩራታቸውን ገልፀው ፤ ስራ ከጀመረበት ከጎርጎሮሳውያኑ 2024 ጀምሮ አሁን ላይ በቀን 550,000 በርሜሎችን በማጣራት እቅዱን ለማሳካት በትክክለኛው መንገድ ላይ እንደሆነ ተናግረዋል። ማጣሪያው የላቁ ቴክኖሎጂዎችን መጠቀሙ እና አለም አቀፍ ደረጃዎችን ማሟላቱ የአለም ገበያን እንዲቀላቀል አስችሎታል ብለዋል።ወደ ሳውዲ አረቢያ የሚላክ ምርት ወሳኝነት ላይ አፅንኦት ሰጥተው የተናገሩት ዳንጎቴ ፤ የነዳጅ ማምረቻው ከፍተኛ ጥራት ያለው የአውሮፕላን ነዳጅ እንደሚያመርት እና ይህም ናይጄሪያ በአለም አቀፉ የኃይል ዘርፍ ላይ ቁልፍ የሆነ ሚና እንዲኖራት ያደርጋል ብለዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0