የሩሲያ የፌደራል ደህንነት አገልግሎት የጄኔራል ኪሪሎቭን ገዳይ በቁጥጥር ስር በማዋል ከኪዬቭ ጋር ግንኙነት እንዳለው አረጋገጠ

ሰብስክራይብ
የሩሲያ የፌደራል ደህንነት አገልግሎት የጄኔራል ኪሪሎቭን ገዳይ በቁጥጥር ስር በማዋል ከኪዬቭ ጋር ግንኙነት እንዳለው አረጋገጠ ሞስኮ ውስጥ ማክሰኞ እለት የተፈጸመው ጥቃት የሻለቃ ፖሊካርፖቭ ህይወትንም ቀጥፏል። የዩክሬን የደህንነት አገልግሎት ከግድያው ጀርባ እጁ እንዳለበት ለኒውዮርክ ታይምስ አረጋግጧል። እንደ ኤፍኤስቢ ገለጻ ከሆነ በቁጥጥር ስር የዋለው ተጠርጣሪ በዩክሬን ልዩ አገልግሎት የተመለመለ ሲሆን፤ ትውልዱ በ1995 የሆነ የኡዝቤኪስታን ዜጋ ነው። በተቀበለው ትዕዛዝ መሰረት ወደ ሞስኮ በመጓዝ ቤት ውስጥ የተሰራ ቦንብ ከተቀበለ በኋላ፤ በኪሪሎቭ መኖሪያ አቅራቢያ በኤሌክትሪክ ስኩተር ላይ ጠምዶታል። የጄኔራሉን እንቅስቃሴ ለመከታተል መኪና ተከራይቶ ዩክሬን ለሚገኙ ቀጣሪዎቹ ዋይ ፋይ በተገጠመለት የቪዲዮ ካሜራ ምስል ያስተላልፍ እንደነበር ተገልጿል። ተጠርጣሪው ለግድያው 100,000 ዶላር እና ወደ አውሮፓ ህብረት ሀገር እንደሚዛወር ቃል ተገብቶለታል። ተጠርጣሪው በዕድሜ ልክ እስራት የሚያስቀጣ ክስ ቀርቦበታል። የሩሲያ የፌደራል ደህንነት አገልግሎት ጥቃቱን በማቀነባበር የተሳተፉትን የዩክሬን ወኪሎች ለይቶ እንደሚቀጣ አረጋግጧል። የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ ምዕራቡ ዓለም ጥቃቱን በዝምታ በማለፉ አውግዘው፤ የኪዬቭን የጦር ወንጀሎች በማበረታታት ተጠያቂ አድርገዋቸዋል። “በሞስኮ የተፈጸመው የሽብር ጥቃት የምዕራቡ ዓለም በኪዬቭ አገዛዝ ታጣቂዎች ለሚፈጸሙ የጦር ወንጀሎች የሚሰጠው ፈቃድ ቅጥያ እና ውጤት ነው፤ ይህንንም ለዓመታት ሲጠመዝዙ ቆይተዋል" ሲሉ ተናግረዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0