የዩክሬን ጦር በምእራባውያን አታሲምስ ሚሳኤል በታጋንሮግ ላይ ላደረሰው ጥቃት አግባብ የሆነ ምላሽ በግዜ ውስጥ ይደረጋል ክሬሚሊን እንዳስታወቀዉ

ሰብስክራይብ
የዩክሬን ጦር በምእራባውያን አታሲምስ ሚሳኤል በታጋንሮግ ላይ ላደረሰው ጥቃት አግባብ የሆነ ምላሽ በግዜ ውስጥ ይደረጋል ክሬሚሊን እንዳስታወቀዉ" በተፈጥሮ ምላሽ ግዜ ያስፈልገዋል በትክክለኛ ሁኔታ እና አግባብ ያለ ምንም ጥርጥር ምላሹ የሚከተል ይሆናል" በማለት የክሬሚሊን ቃል አቀባይ ዲሜትሪ ፔስኮቭ ለሪፖርተሮች ተናግረዋል።ይህ በሩሲያዋ የደቡብ ከተማ ታጋንሮግ በሚገኝ የጦር  አውሮፕላን ሜዳ ላይ በትላንትናው እለት የተፈፀመው ጥቃት 6 አታሲምስ ሚሳኤሎችን በመጠቀም እንደሆነ የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል። 2 ሚሳኤሎች ተመተው የወደቁ ሲሆን ቀሪዎቹ በኤሌትሪክ ጦር መሳሪያ አቅጣጫቸውን እንዲቀይሩ ተደርጓል። ተመቶ በወደቀዉ ሚሳኤል ፍንጥርጣሪዎች ሰዎች ተጎድተዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0