የኢትዮዽያ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር በአፍሪካ ቀንድ መረጋጋት እንዲሰፍን ጠየቁ

ሰብስክራይብ
የኢትዮዽያ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር በአፍሪካ ቀንድ መረጋጋት እንዲሰፍን ጠየቁታዬ አፅቀስላሴ የአፍሪካ ህብረት በሶማሊያ የሽግግር ተልዕኮ (ኤቲኤምአይኤስ) ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ ሽግግርማድረግ እንደሚያስፈልግ አፅንዖት ሰጥተዋል። "የአፍሪካ ህብረት በሶማሊያ የሽግግር ተልዕኮ የአፍሪካ ቀንድ ወደ ከፍተኛ አለመረጋጋት እና ትርምስ ሊያመራ እንደማይገባ ግልፅ እናድርግ። ከሁሉም በላይ ደግሞ በጣም አደገኛ  በሆኑ አህጉራዊ እና አለምአቀፍ አሸባሪ ቡድኖች ላይ የተገኘውን ጠንካራ ድል ማኮስመን የለበትም" ሲሉ በ ኤክስ ገጻቸው ላይ ጽፈዋል።ቀጠናው ወሳኝ ለውጦች ሲያጋጥሙት፤ ሽብርተኝነትን በመዋጋት የተገኘውን ስኬት መጠበቅ እና ለወደፊቱም መረጋጋት እና ደህንነትን ማረጋገጥ አስፈላጊ መሆኑን ሚንስትሩ አስምረውበታል።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0