በጸጥታ ስጋት ውስጥ የምትገኘው ናይጄሪያ አዳዲስ የደህንነት ሃላፊዎችን ሾመች ፕሬዝዳንት ቦላ ቲኑቡ የቀድሞው ኃላፊዎች ባሳለፈነው ሳምንት በድንገት ከሃላፊነታቸው መልቀቃቸውን ተከትሎ ለብሔራዊ መረጃ ኤጀንሲ (NIA) እና የሀገር ደኅንነት ክፍል (DSS) አዲስ ኃላፊዎችን ሾመዋል። ቀደም ሲል በሊቢያ የናይጄሪያ አምባሳደር የነበሩት መሐመድ መሐመድ የብሔራዊ መረጃ ኤጀንሲ ኃላፊ ሆነው የተሾሙ ሲሆን አዴላ አጃዪ የሀገር ደኅንነት ክፍሉን እንዲመሩ ተመርጠዋል። እ.አ.አ. በ2018 በቀድሞው ፕሬዝዳንት ሙሃማዱ ቡሃሪ የተሾሙት የቀድሞው ኃላፊዎች ለስራ መልቀቂያቸው ምክንያት አላቀረቡም ተብሏል። ሹመቱ በናይጄሪያ ከፍተኛ የጸጥታ ስጋት ባየለበት ወቅት የመጣ ነው። በሰሜን ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍል ለአስርት ዓመታት የዘለቀው የአመጽ እንቅስቃሴ እና በታጠቁ ወንጀለኞች የሚፈጸመውን አፈና ጨምሮ ሀገሪቱ ዘርፈ ብዙ የጸጥታ ስጋት ውስጥ ትገኛለች። እነዚህን ስጋቶች ለመዋጋት እና በመላ ሀገሪቱ ያለውን ደህንነት ለማሻሻል በሚደረገው ጥረት ፕሬዝዳንት ቲኑቡ መረጃ መሰብሰብ ዋነኛ ጉዳያቸው ነው ተብሏል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
በጸጥታ ስጋት ውስጥ የምትገኘው ናይጄሪያ አዳዲስ የደህንነት ሃላፊዎችን ሾመች
በጸጥታ ስጋት ውስጥ የምትገኘው ናይጄሪያ አዳዲስ የደህንነት ሃላፊዎችን ሾመች
Sputnik አፍሪካ
በጸጥታ ስጋት ውስጥ የምትገኘው ናይጄሪያ አዳዲስ የደህንነት ሃላፊዎችን ሾመች ፕሬዝዳንት ቦላ ቲኑቡ የቀድሞው ኃላፊዎቹ ባሳለፈነው ሳምንት በድንገት ከሃላፊነታቸው መልቀቃቸውን ተከትሎ ለብሔራዊ መረጃ ኤጀንሲ (NIA) እና የሀገር ደኅንነት ክፍል (DSS)... 27.08.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-08-27T19:20+0300
2024-08-27T19:20+0300
2024-08-28T12:08+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий