ዴንማርክ በቡርኪናፋሶ እና ማሊ በተካሄደው ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ምክንያት በሀገራቱ የሚገኙትን ኤምባሲዎቿን እንደምትዘጋ ገለጸች

ሰብስክራይብ
ዴንማርክ በቡርኪናፋሶ እና ማሊ በተካሄደው ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ምክንያት በሀገራቱ የሚገኙትን ኤምባሲዎቿን እንደምትዘጋ ገለጸች "በተካሄዱት ተከታታይ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥቶች ሳቢያ በሳህል ቀጠና የንግድ ቦታ ውስንነት በመፈጠሩ በቡርኪናፋሶ እና ማሊ የሚገኙት ኤምባሲዎች ይዘጋሉ" ሲል የዴንማርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመግለጫው አስታውቋል። ዴንማርክ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ያላትን ትብብር ለማስፋት ባዘጋጀችው አዲስ የውጭ ፖሊሲ ስትራቴጂ መሰረት በሴኔጋል፣ ቱኒዚያ እና ሩዋንዳ ኤምባሲዎችን እንደምትከፍት ሚኒስቴሩ አክሎ ገልጿል። በተጨማሪም ኮፐንሄገን በግብፅ፣ ኬንያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ናይጄሪያ እና ጋና በሚገኙ ሚሲዮኖቿ የዲፕሎማሲ "ኃይሏን" እንደምታጠናክር መግለጫው አመልክቷል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0