የሩሲያ ሲኒማ ቀን በአዲስ አበባ ሊከበር ነው

ሰብስክራይብ
የሩሲያ ሲኒማ ቀን በአዲስ አበባ ሊከበር ነውበየአመቱ በነሀሴ መጨረሻ የሚካሄደውን እና በሩሲያ ፌዴሬሽን ውስጥ ከሚገኙ የሲኒማቶግራፈር ባለሙያዎች እና የፊልም አፍቃሪያን ሙያዊ የበዓል ቀን ጋር ተያይዞ የሚከበረውን የመላው ሩሲያ ሲኒማ ምሽት ኢትዮጵያ ተቀላቀላለች። የዚህ አመት ዝግጅቱ በሌሎች የብሪክስ ሀገራትም ይከናወናል። "የሲኒማ ምሽት ለመጀመሪያ ጊዜ በአለም አቀፍ ደረጃ ይከናወናል። የሩሲያ  ፊልሞች በህንድ፣ በቻይና፣ በብራዚል፣ በኢትዮጵያ፣ በግብፅ የሚታዩ መሆናቸውን የሩሲያ የባህል ሚኒስትር ኦልጋ ሊቢሞቫ ተናግረዋል።በዓሉን ምክንያት በማድረግ አዲስ አበባ በሚገኘው ፑሽኪን የባህል ማዕከል ከሰዓት በኋላ 10፡00 ጀምሮ የእንግሊዝኛ ሰብ ታይትል ያላቸው ሶስት የሩሲያ ፊልሞች በነጻ ይታያሉ። እ.ኤ.አ ነሐሴ 18 ቀን የሩሲያ የሳይንስ እና የባህል ማዕከል እንግዶች የሳይንስ ይዘት ያለውን "የወደፊቱ እንግዳ"፣ "የዓሣ ምኞት ተረት" እና "አየር" የተሰኘውን ወታደራዊ-ታሪካዊ ድራማ ማየት ይችላሉ።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0