ሱዳን እና ሩሲያ የንግድ ግብይታቸውን በሀገር ውስጥ መገበያያዎች ለመፈጸም ተስማሙ

ሰብስክራይብ
ሱዳን እና ሩሲያ የንግድ ግብይታቸውን በሀገር ውስጥ መገበያያዎች ለመፈጸም ተስማሙ የሩሲያ ማዕከላዊ ባንክ የልዑካን ቡድን ከሱዳን ማዕከላዊ ባንክ ገዥ ቦራይ አል-ሲዲቂ ጋር ሱዳን ውስጥ ውይይት አካሂዷል። የውጭ ምንዛሪ ጥገኝነትን ለመቀነስ የሀገር ውስጥ ገንዘቦችን በንግድ ልውውጦች ላይ መጠቀምን በተመለከተ እንዲሁም በሌሎች ጉዳዮች ዙርያ ተወያይተዋል። የሀገሪቱ ይፋዊ የዜና ወኪል ሱና እንደዘገበው የሩሲያ ልዑካን ቡድን ወርቅን ጨምሮ በከበሩ ማእድናት ዘርፍ የጋራ ኢንቨስትመንት ስለመፍጠር ተወያይቷል። የሱዳን እና ሩሲያ ባንኮች እነዚህን ፕሮጀክቶች ፋይናንስ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። በሁለቱ ሀገራት ቅርንጫፎችን በመክፈት የንግድ ልውውጦችን ለመደገፍ እና የወጪና ገቢ ንግድን ለማሳደግ እንደታሰበም ታውቋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0