የመንግሥታቱ ድርጅት የንግድና ልማት ኤጀንሲ የኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ የኢንቨስተሮችን መተማመን የሚያጎለብት ነው ሲል አወደሰ ፖሊሲው የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ለማጠናከር እና የውጭ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ አወንታዊ እርምጃ ነው ሲል የተባበሩት መንግሥታት የንግድና ልማት ጉባኤ (UNCTAD) አወድሶታል። የኤጀንሲው የአፍሪካ ክልል ጽህፈት ቤት ኃላፊ ዳያን ሳይንዞጋ ፖሊሲው መዋቅራዊ የኢኮኖሚ ተግዳሮቶችን ለመፍታት እና የኢትዮጵያን የንግድ ምህዳር ከቀጠናው ኢኮኖሚ ጋር ለማጣጣም አቅም እንዳለው አመልክተዋል። "ይህ በጣም አወንታዊ እርምጃ ነው። የሀገሪቱን የማክሮ ኢኮኖሚ ምህዳር ከማጠናከር እና የባለሃብቶችን እምነት ከማሳደግ አንጻር በመጪዎቹ ወራት እጅግ አዎንታዊ ውጤት ያስገኛል" ሲሉ ሳይንዞጋ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሪ ስርዓት በመቀየር የለውጥ ፖሊሲውን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ማድረግ ጀምሯል። እንደ የሀገሪቱ ማዕከላዊ ባንክ ገለጻ ማሻሻያው ከፍተኛ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት (FDI) ይስባል ተብሎ ይጠበቃል። በምንዛሪ ተመን ላይ ይደረግ በነበረ ቁጥጥር እና በውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት እጥረት ባለሀብቶችን በማሸሽ ተቸግራ በነበረችው ኢትዮጵያ ማሻሻያው ስር ነቀል ለውጥ ተደርጎ ተወስዷል።ሳይንዞጋ አያይዘውም መንግሥት ምቹ የኢንቨስትመንት ሁኔታን ለመፍጠር ያሳየው ቁርጠኝነት ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር የረጅም ጊዜ የትብብር ታሪክ ያላቸው እንደ የተባበሩት መንግሥታት የንግድና ልማት ጉባኤ ያሉ ዓለም አቀፍ ድርጅቶችን እንደሚያበረታታ እና ባለሀብቶችንም እያነሳሳ እንደሆነ ጠቁመዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የመንግሥታቱ ድርጅት የንግድና ልማት ኤጀንሲ የኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ የኢንቨስተሮችን መተማመን የሚያጎለብት ነው ሲል አወደሰ
የመንግሥታቱ ድርጅት የንግድና ልማት ኤጀንሲ የኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ የኢንቨስተሮችን መተማመን የሚያጎለብት ነው ሲል አወደሰ
Sputnik አፍሪካ
የመንግሥታቱ ድርጅት የንግድና ልማት ኤጀንሲ የኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ የኢንቨስተሮችን መተማመን የሚያጎለብት ነው ሲል አወደሰ ፖሊሲው የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ለማጠናከር እና የውጭ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ አወንታዊ እርምጃ ነው ሲል የተባበሩት... 18.08.2024, Sputnik አፍሪካ
2024-08-18T11:28+0300
2024-08-18T11:28+0300
2024-08-18T11:46+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2024
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
የመንግሥታቱ ድርጅት የንግድና ልማት ኤጀንሲ የኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ የኢንቨስተሮችን መተማመን የሚያጎለብት ነው ሲል አወደሰ
11:28 18.08.2024 (የተሻሻለ: 11:46 18.08.2024)
ሰብስክራይብ