"ቻድ በፍጹም እጅ አትሰጥም"

ሰብስክራይብ
"ቻድ በፍጹም እጅ አትሰጥም" የቻድ ፕሬዝዳንት ነሐሴ 5 ቀን የተከበረውን 64ኛ ዓመት የነፃነት በዓል ምክንያት በማድረግ የተናገሩት ነው። ማሃማት ኢድሪስ ዴቢ ኢቶኖ ጣታቸውን “የራሳችንን ወገኖች ለድብቅ አላማቸው መሳካት የሚጠቀሙ የውጭ ወኪሎች” ብለው በገለጿቸው ላይ ቀስረዋል። በውጭ ጥቅም ለመሳብ የሚፈቅዱ "እንዲሰበስቡም” ጠይቀዋል። "የሪፐብሊኩ ፕሬዝዳንት እና ለሀገሪቱ ሉዓላዊነት ዋስተና እንደመሆኔ የቻድን ሉዓላዊነት ለመጠበቅ ህይወቴን ከመሰዋት ወደ ኋላ አልልም " ብለዋል። በግንቦት ወር በፕሬዝዳንትነት የተመረጡት ዴቢ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ማፋጠን፣ የመጠጥ ውሃ ማቅረብ፣ ሆስፒታሎችን መገንባት እና ማደስ እና የትምህርት ስርዓቱን ማጠናከር “የፖለቲካ ፕሮግራማቸው” አካል እንደሆነም ተናግረዋል። ሙስናን ለመዋጋት ቁርጠኛ እነደሆኑ የገለጹት ፕሬዘዳንት ዴቢ ኢትኖ የሀገሪቱ "መራር እውነታ" ነው ብለውታል። "ይህን አስከፊ ችግር ለመታገል የምናደርገው ትግል ሁሉን አቀፍ ነው። መንግሥት የህዝብ ሃብት ምዝበራን የማይታገስ ፖሊሲ ስራ ላይ እንዲያውል መመሪያ ተሰጥቶታል።" ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0