ሩሲያ ለአንጎላ 50 አምቡላንሶችን ለገሰች

ሰብስክራይብ
ሩሲያ ለአንጎላ 50 አምቡላንሶችን ለገሰች በአንጎላ የሩሲያ አምባሳደር ቭላድሚር ታራሮቭ የሩሲያ ሞዴል የሆኑትን ጋዜል ቢዝነስ 4x4 ተሽከርካሪዎች ለሀገሪቱ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ሲልቪያ ሉቱኩታ አስረክበዋል። የአምቡላንሶቹ ድጋፍ ሩሲያ ለአንጎላ ሕዝብ የምታደርገው የሰብዓዊ ዕርዳታ አካል እንደሆነ የሩሲያ ኤምባሲ በቴሌግራም ቻናሉ ገልጿል። የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ጃዎ ሎሬንሶ ለሩሲያ አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ባቀረቡት የግል ጥያቄ መሰረት ተሽከርካሪዎቹ ወደ አንጎላ በነፃ እንደተላኩ ታራሮቭ ጠቁመዋል። 685,500 ዶላር የሚጠጋ ወጪ የተደረገበት የሰብዓዊ ፕሮጀክት የሩሲያ መንግሥት በዚህ ዓመት በአፍሪካ አህጉር ካከናወናቸው ትልቅ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ እንደሆነም ተናግረዋል። ከሩሲያ ህዝብ እና መንግሥት የተገኘው ይህ ስጦታ አንጎላውያንን ለረጅም ጊዜ እና በአስተማማኝ ሁኔታ እንደሚያገለግል እና ያስቀረው ወጪ የብሔራዊ ጤና አገልግሎት ስርዓቱን ለማሻሻል ይውላል ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0