የነሐሴ 2 ረፈድ ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች

ሰብስክራይብ
የነሐሴ 2 ረፈድ ዋና ዋና  የዓለም ዜናዎች  🟠 በሩሲያ ኩርስክ ክልል በዩክሬን በተፈፀመ ጥቃት 5 ህፃናትን ጨምሮ በድምሩ 34 ተጎጂዎች በሆስፒታል ህክምና ላይ እንደሚገኙ የሩሲያ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ኃላፊ ረዳት ገልጿል።  🟠 የሩሲያ ቪጂቲሪክ ብሮድካስቲንግ ካምፓኒ የጦርነነት ዘጋቢ ጋዜጠኛ ዬቭጊኒ ፖዱብኒ መቁስሉን ተከትሎ ከኩርስክ ወደ ሞስኮ ለተጨማሪ ህክምና መላኩን ተጠባባቂው ገዥው አስተውቀዋል ። 🟠 የቀድሞ የአሜሪካ የስለላ ሀላፊ ስኮት ሪትተር በመኖሪያ ቤቱ ፍተሻ እየተደረገ ያለው ከሩሲያ መገናኛ ብዙሃን ጋር ባለው ትብብር እንደሆነ ገልፆ፤ ይህ "የማስፈራራት" ተግባር ነው ሲል ተናግሯል።  🟠 የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባይደን ትራምፕ ከተሸነፉ በዩናይትድ ስቴትስ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ሂደት ላይ እርግጠኛ እንዳልሆኑ ተናግረዋል። 🟠 ዋሽንግተን አውሮፓ የመከላከል ግዴታ የለባትም። እንደ ጀርመን ያሉ ሀገራት በራሳቸው መከላከያ ላይ ኢንቨስት በማድረግ በወታደራዊ ዘርፍ ራሳቸውን መቻል አለባቸው ሲሉ የአሜሪካ ሪፐብሊካን ፓርቲ እጩ ምክትል ፕሬዝዳንት ቫንስ ተናግረዋል።ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0